ad

የተመረጠው ኢህአዴግ እንጂ ብልጽግና አይደለም-ዶ/ር ሰለሞን ኪዳነ

የ ህወሃት ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል እና የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር የነበሩት ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብረ እግዚአብሄር በጠቅላይ ሚንስትሩ ሹም ሽር ከስልጣናቸው ከተነሱት መካከል ተጠቃሽ ናቸው።

በተመሳሳይ የህወሃት ከፍተኛ አመራር የሆኑት በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊው ሰለሞን ኪዳነ (/) ከስልጣን እንደሚነሱ ደብዳቤ እንደደረሳቸው ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ይህን ተከትሎ ህወሃት ባወጣው መግለጫ አባላቱን ከፌደራል ከፍተኛ የሃላፊነት ደረጃዎች እንዲሁም ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የማንሳት እርምጃ ህግን የጣሰና ችግርም የሚያስከትል ነው ብሏል።
ብልፅግና ፓርቲ በበኩሉ የተደረገው የተለመደ ሹም ሽር ስለሆነ ከብሄር እና ከፖለቲካ ጋር ማገናኘት አይገባም ሲል ምላሽ ሰጥቷል።

ሰለሞን ኪዳነ (/) በአዲስ አበባ በክፍለ ከተማ ደረጃ የሚገኙ የህወሓት ካድሬዎችና የስራ ኃላፊዎች በጠቅላይ ሚኒስትር /ቤት እየተነሱ በሌሎች አባል ባልሆኑ እየተተኩ ነው ብለዋል። "አዲስ አባባ ላይ እንደ ኢህአዴግ ነው የተወዳደርነው። ኢህአዴግ እስካሸነፈ ድረስ ህወሓት 25 በመቶ ቦታ፤ እኩል የማስተዳደር ስልጣን አለው። ይህንን አሰራር ማፍረስ ማለት የከተማውን መንግሥታዊ አስተዳደር መዋቅር ማፍረስ ማለት ነው" በማለትም እርምጃው ህግና ስርዓትን የተላለፈ ነው ይላሉ። ላለፉት 28 ዓመታት ስልጣን ላይ የቆየው ኢህአዴግ ወደ ብልጽግና ፓርቲ ሲሸጋገር ስሙን ብቻ ሳይሆን ርእዮተ ዓለሙን አብዮታዊ ዲሞክራሲን በመደመር ጽንሰ ሃሳብ ቀይሯል። ህወሃት ይህ ሂደት ህገ-ወጥ ነው በማለት ብልፅግናን የማይቀላቀል መሆኑንን ማሳወቁ በፌደራል መንግሥትና በትግራይ ክልል መንግስት መካከል የተፈጠረውን ልዩነት ይበልጥ እንዳካረረው እየተስተዋለ ነው።