ad

የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እየተፈጠሩ ያሉት በመንግስት ሳይሆን የተለያየ የፖለቲካ አስተሳሰብ ባላቸው ቡድኖች ነው

Image result for ዳንኤል በቀለ
የ ሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እየተፈጠሩ ያሉት በመንግስት ሳይሆን የተለያየ የፖለቲካ አስተሳሰብ ባላቸው ቡድኖች ነው - / ዳንኤል በቀለ በኢትዮጵያ ግጭቶች እየተፈጠሩ ያሉት በመንግስት ሳይሆን የተለያየ የፖለቲካ አስተሳሰብ ባላቸው ቡድኖችና ግለሰቦች መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ባለስልጣን የሆኑት አቶ ዳንኤል በቀለ ዘግበዋል
/ ዳንኤል በቀለ እንዳሉት በተለያዩ አካባቢዎች እየተፈጠሩ ላሉ ችግሮች መነሻቸው መንግስት ሳይሆን የተለያዩ የፖለቲካ ፍላጎት ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ናቸው።
በተወሰኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚራመዱ የፖለቲካ አስተሳሰቦች በአገሪቱ ለሚስተዋሉ አመፅና ግጭቶች ዋናኛ ምክንያቶች መሆኑን ያሰመሩበት ኮሚሽነሩ በተለይ የፖለቲካ ፍላጎቶች፣ ከማንነትና ከወሰን ጋር የተያያዙ ጥያቄዎች፣ ሃይማኖታዊ ጉዳዮች አገሪቱን ለቀውስ እንደዳረጓት ነው ብለዋል።
እንደ ዋና ኮሚሽነሩ ገለፃ ከዚህ በፊት ሰብአዊ መብት ጥሰት ይካሄድ የነበረው በፖሊስና በፀጥታ ሀይሎች ነበር ይሁንና አሁን ላይ ሁኔታዎች ተለውጠው የፖለቲካ ፍላጎት ባላቸው ሃይሎች ምክንያት ነው።